ለመጸለይ አንፍራ

📌 ለመጸለይ አንፍራ ❖ ኃጢያተኛ ነኝ … በእግዚአብሔር ፊት የሚያስቆም ስብዕና የለኝም…. ዘማዊ ነኝ… ሰካራም ነኝ…. ዘፋኝ ነኝ…. ምንም አይነት የፀሎት ቋንቋ አልችልም…. ምን ተብሎም እንደሚፀለይ አላውቀበትም ብለህ ወደ እግዚአብሔር መፀለይን አትፍራ... በዚህ የፆም ወራት ፀሎትን ማድረስ ቸል አትበል። ❖ ሠው ያላደረገውን ኃጢያት አድርጌያለሁ ብለህ ፀሎትን ማቅረብ ቸል አትበል፤ እግዚአብሔርን ክጄዋለሁ…. እንዴት ብዬ ነው ፊቱ የምቆመው ? ብለህ መፀለይ አትፍራ ፡፡ ❖ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን አልክድህም ብሎ ከተናገረ በኋላ ጌታችንን ካደው "የምትይውን ሰው አላውቀውም በሎ በህዝብ ፊት ካደ" ከአንዲት ገረድ ንግግር ጌታችንን አንስቶበት ካደ፤ ሁለተኛም በቅፅር ተቀምጦ ሳለ "አላውቀውም " ብሎ ማለ፤ ሦስተኛም ልብሱን ጥሎ እስኪሸሽ ድረስ "የምትሉትን ሰው አላውቀውም ብሎ ማለ" ፡፡ ❖ ይህን ጊዜ ዶሮ ጮኽ ጌታም ትክደኛለህ ብሎ የተናገው ትዝ አለው ይህን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ጌታ ለመፀለይ አልፈራም ፡፡ ❖ ቅዱስ ዳዊት ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ አስገድሎ ሚስቱን አግብቶ ሲያበቃ የነብዩን ቃል ሲሰማ በእግዚአብሔር ፊት ስቅስቅ ብሎ ለማልቀስ አልፈራም እግዚአብሔር ይለመነው ዘንድ ለመፀለይ አልፈራም። ❖ አባታችን አዳም በገዛ ፍቃዱ ተመርቶ ገነትን ታክል ቦታ እግዚአብሔርን የመሰለ አባት አጥቶ ሲያበቃ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፤ በእግዚአብሔር ፊት በየሱባዔው ለመፀለይን አልፈራም፤ እኛም በምንም ሁኔታ እንሁን በምን በእግዚአብሔር ፊት መጸለይን አንፍራ፡፡ ❖ የሁላችንን ድካም የሚያውቅ እግዚአብሔር ነውና፤ ለመጸለይ ዛሬ እንነሳ አንፍራ።

Comments

Popular posts from this blog

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ